የሞት ፍልስፍና በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች ውስጥ

Authors

  • Desalegn Seyoum Addis Ababa University

Abstract

አጠቃሎ፦ ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው ከአራት የግጥም ሥራዎች የተመረጡ አራት ግጥሞች ላይ ነው። ግጥሞቹ ነቢይ መኮንን፤ ፀሐይ መላኩ፤ አበባው መላኩና አንዷለም አባተ ጸጋዬ ገብረ መድኅንን ለመዘከር የገጠሟቸው ግጥሞች ናቸው። ግጥሞቹ ሊመረጡ የቻሉት ሞትን በፍልስፍና ዕይታ በማዬታቸው ለጥናቱ ጉዳይ ቀጥተኛ ተተኳሪ ሊሆኑ በመቻላቸው ነው። በጥናቱ የተፈተሹት፤ የተመረጡትም ጉዳይ-መር (purposive) ዘዴን በመጠቀም ነው። የጥናቱ ዓላማ ገጣሚዎቹ ምን ዓይነት የሞት ፍልስፍናን እንደሚከተሉ ማሳዬት ነው። በጥናቱ ማረጋገጥ እንደተቻለው አራቱ ገጣሚያን የተለያዩ የሞት ፍልስፍናዎችን ይከተላሉ። ፍልስፍናቸውም ‹ከሞት በኋላ ሕይወት› እና ‹ሞት የመጨረሻ› በሚሉት ሁለት ጥቅል የሞት ፍልስፍና ጥላዎች ውስጥ ማረፍ ቢችሉም ገጣሚያኑ የየራሳቸው ዝርዝር የሞት ፍልስፍና እንዳላቸው ማረጋግጥ ተችሏል። 

Downloads

Published

2024-03-15