በቱለማ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት እንስትነትን የሚገልፁ የከበሩ ንዋያት ትዕምርታዊ ጥናት[1]
Abstract
አጠቃሎ
የዚህ ጥናት ዓላማ በቱለማ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት እንስትነትን የሚያመለክቱ ትዕምርቶችን በትንታኔ ማሳየት ነው፡፡ በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት የከበሩ ንዋያት የቱለማ ኦሮሞን ባህል እና ወግ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት በተለይም ከእንስትነት እና ከትዕምርት ብሎም ከሥርዓተ ከበራ አንፃር አልተጠኑም፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ምርምርን የተከተለ ሲሆን፣ ገላጭ የአጠናን ስልትን ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በቃለ መጠይቅ፣ በመስክ ምልከታ እና በተተኳሪ የቡድን ውይይት የተሰበሰቡ ቀዳማይ መረጃዎች ከልዩ ልዩ ስነዘዴዎች፣ ፅንሰ ሃሳባዊ እና ንድፈ ሃሳባዊ ማዕቀፎች ጋር ተዋህደው ተተንትነዋል፡፡ መረጃዎቹ ስለ ጫጩ፣ ጨሌ፣ ሲንቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚያወሱ ናቸው፡፡ በትንታኔው እንደታየውም በገዳ ሥርዓት ውስጥ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው እነዚህ እንስትነትን የሚያመለክቱት የከበሩ ንዋያት ባላቸው ትዕምርታዊ ፍቺ የሴቶችን ማህበራዊ ደረጃ እና ሚና፣ ክብር፣ ተቀባይነት እና ተደማጭነትን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ ከትዕምርታዊ ፍቺ አንፃር ደግሞ እንስትነትን እና መራባትን የሚገልፁ ሲሆን ዕርቅ ለመፈፀም እና ግጭቶችን ለማስወገድ ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡
የጥናቱ ቁልፍ ቃላት፡- [እንስትነት፣ ትዕምርት፣ ጫጩ፣ ጨሌ፣ ሲንቄ]፡፡
Downloads
Published
2024-02-25
How to Cite
Tadese Beriso, G. K. 1. (2024). በቱለማ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት እንስትነትን የሚገልፁ የከበሩ ንዋያት ትዕምርታዊ ጥናት[1] . ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 32(2), 85–113. Retrieved from http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/9489
Issue
Section
Articles