በግዕዝ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ሰዋስዋዊ ግድፈቶችና ትርጓሜው የተጠቀመባቸው ሥነ ጽሑፋዊ የማቅኛ ሥልቶች

Authors

  • Senkoris Ayalew

Abstract


የዚህ ጥናት ዋና ቁም ነገር በአንድምታ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ የግዕዝ አገባባዊ ስሕተቶችን
(ከዘመኑ የቋንቋ አጠቃቀም አንፃር) እንዴት ማቅናት እንደተቻለ ማሳየት ሲሆን ጥናቱም
ዐይነታዊ ምርምርን የሚከተል ሆኖ የገለፃ ስልትን የሚጠቀም ነው፡፡ በመረጃ ባለቤትነትም
የኢትዮጵያውያን የአንድምታ መጻሕፍትን እንዲሁም የሊቃውንትን ሐሳብ በመጠይቅ ስልት
በመረጃ ቋትነት አካትቷል፡፡ አማርኛውም ‘‘ግድፈት’’ ለተሰኘው ሥርዓተ ልሳን ከግዕዙ አገባብ
ጎን ለጎን ትንታኔ በመስጠት አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ በጥናቱ ውስጥም
እነዚህ አንድምታዎች በቋንቋ ዕይታ ሲቃኙ ያላቸውን የሥነ ጽሑፍ እድገትና ሚና በጥልቀት
ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ የአንድምታ ጽሑፎች እስከ ማብራሪያቸው ድረስ
ሀገር በቀል መሆናቸውንና በየትኛው ዘመን ጎልተው ለጽሑፍ ሀብትነት እንደቀረቡ ጥናቱ
ጠቁሟል፡፡ በመጨረሻም ለማስረጃ የተመረጡ ማሳያዎችን ከመጻሕፍቱ በመልቀምና በመተንተን
የሚያስረዳ ሲሆን ይህ ፈርጀ ብዙ የሆነውና ያልተጠናው የአንድምታ ሀብትም የበለጠ ምርምርና
ጥበቃ እንደሚያስፈልገው በመጠቆም ሐሳቡን ይደመድማል፡፡

Downloads

Published

2024-03-04

How to Cite

Senkoris Ayalew. (2024). በግዕዝ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ሰዋስዋዊ ግድፈቶችና ትርጓሜው የተጠቀመባቸው ሥነ ጽሑፋዊ የማቅኛ ሥልቶች . ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 29(1), 62–83. Retrieved from http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/9690