ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures) http://213.55.95.79/index.php/JAELC
The Zena-Lissan Journal was started in 1996 by the then Ethiopian Languages Research Centre (ELRC), now the Academy of Ethiopian Languages and Cultures (hereafter AELC), focused especially on the cultures (folklores) and languages of different societies within Ethiopia. Since then, the journal has continued to be published biannually in Amharic and English languages aimed to encourage research and promote dialogue among scholars of interdisciplinary fields.
en-US Tue, 05 Nov 2024 08:16:43 +0000 OJS 3.2.1.3 http://blogs.law.harvard.edu/tech/rss 60 Social Deictics in the Arsi-Bale Dialect of Oromo http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10659

The main objective of this study is to investigate and describe the forms and functions of social deictics in Arsi-Bale dialect of Oromo[3] which is spoken in the southeastern part of Ethiopia. Social deictics are the means to encode verbal pointing in a speech event taking into account the relationship or social status between a speaker, an addressee, and a non-participant. The study is a qualitative one for which data were collected through note-taking of free language use, elicitation and introspection. The findings show that social deictics in the dialect are encoded lexically and grammatically. While relational kinship terms (e.g., ʔabba: ‘father/dad’), expressions signalling social status (e.g. ʃeːka ‘sheikh’) and personal names are used for lexical encoding, plural personal pronouns and the corresponding agreement marking on predicate verbs are used for grammatical encoding. Among some speakers of the dialect, reference to certain phenomena which are considered sacred (water, fire, grass, etc.)  is encoded with the third person plural agreement marking of the predicate verb.

[Keywords: absolute, honorific, kinship term, relational, social deictic]

Ahmed Mahmud [1] and Shimelis Mazengia[2] Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10659 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000 A Survey of the Linguistic Development of Sidaama http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10660

Most of the written use of Sidaama in the pre-1991 period was a liturgical one. It was the post 1993 period that witnessed a tremendous development. Hence the objective of this paper is describing the linguistic development of Sidaama with a particular emphasis in the last three decades. First of all, a Latin script was adopted for writing the language while before 1993 it was written in Ethiopic script. Moreover, since 1993 it became a language of instruction in the first cycle of primary schools and then it was taught as a subject. In addition, it begun to be used as an administrative and court language. Furthermore, it became a language of mass media, first in radio broadcasts and since 2015 in TV broadcast. A diploma in Sidaamu Afoo began to be offered at Hawaasa Teachers’ Training College in 2010. In 2013 a B.A.in Sidaamu Afoo and Literature was launched at Hawaasa University and in 2020 a B.Ed. in the same discipline. The language expanded as thousands of neologisms were incorporated and also several books that deal with literary and cultural wealth of the language were published. The language also witnessed development in the sphere of arts and consequently hundreds of songs were recorded. In addition, a theatre troupe was formed that staged dramas based on various genres.

Keywords: [Ethiopia, Sidaama, Cushitic, Highland East Cushitic, linguistic development
Anbessa Teferra[1] Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10660 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000 Clausal Complementation in Dizin http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10661

This paper examines clausal complementation in Dizin, one of the least studied languages in the Southwest part of Ethiopia. The study focuses on the Maji dialect. It describes clausal complements and their functions in light of Noonan (2007) and others’ cross-linguistic observation. The study follows a qualitative research approach based on basic linguistic theory, which advocates the description of a language on its own properties. The data were collected using elicitation from key consultants and from natural texts like fables in Maji district. The findings show that Dizin has finite, infinitive and nominalized complement clauses. The study also shows that the position of these complement clauses is fixed, that is, clausal complements occur left-adjacent to the matrix predicate. The study further shows that finite complement clause and nominalized complement clauses occur in object and subject slots, while infinitive complement clause appears only in object slot. Moreover, it is found that Dizin is right-headed language in the typology of clausal complementation.

Keywords [Clause, predicate, complementation, slot]

Bizualem Amlak[1] Girma Mengistu[2] Desalegn Hagos [3] Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10661 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000 በአዲሱ የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስና በአባ ገሪማ ወንጌል (I) መካከል የተስተዋለ የቋንቋ አጠቃቀም ንጽጽራዊ ጥናት http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10662

አኅጽሮተ ጽሑፍ

ይህ ጥናት በአባ ገሪማ ወንጌል (I) እና በአዲሱ የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ መካከል የተደረገ ንጽጽራዊ ጥናት ነው። ዋና ዓለማዉም በኹለቱ መካከል ያለዉን ልዩነትና በአሁኑ ሰዓት የተረሱ የሰዋስው አጠቃቀም፣ የፊደላት ቅርፅ፣ የፊደልና የስም አጠራር ለውጥ፣ የአሉታ፣ የቅጽል እና የአገባብ አጠቃቀም፣ እንዲሁም የአንዳንድ ቃላትን የአጻጻፍ ለውጥ በንጽጽር ለማጥናት እና ልዩነቱን አጉልቶ ለማሳየት ነው። ይህንንም ጥናት ለማጥናት በዋናነት የተመረጠዉ የጥናት ዘዴ ዓይነታዊ የጥናት ዘዴ ሲኾን መረጃዉም የተሰበሰበዉ በሰነድ ፍተሻ ነው። የአባ ገሪማ ወንጌል ገጾቹ የተገነጣጠሉ እንደ መኾናቸው መጠን ሙሉ የኾኑ ገጾች በዓላማ ተኮር ተመርጠዋል። መረጃዉ የተተነተነዉም ንጽጽራዊ በኾነ መልኩ ገላጭ የትንተና ዘዴን በመጠቀም ነው። በዚህም ጥናት የአባ ገሪማ ወንጌል (1) እና በ2014 የታተመው አዲሱ የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ ከተነጻጸሩ በኋላ የሰዋስው አጠቃቀም፣ የፊደላት ቅርፅ፣ የድምፅና የስም ለውጥ፣ የአሉታ፣ የቅጽል እና የአገባብ አጠቃቀም፣ እንዲሁም የአንዳንድ ቃላት የአጻጻፍ ለውጥ በሰፊዉ ተገኝቷል። ይህንም በሁለቱ መካከል ያለዉን ልዩነት አዲስ ግኝት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ምክንያቱም በዚህ ዘመን ያሉ የግእዝ ምሁራን በአባ ገሪማ (1) የተጠቀሱትን እንደማይጠቀሙባቸው በጥናቱ ተረጋግጧል። በዚህ አጋጣሚ በግእዝ ላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ምሁራን ገሪማ (I)፣ ገሪማ (II) እና ገሪማ (III) ላይ ጥልቅ ጥናት ቢያካኺዱ ሌሎች መሰል ልዩነቶች ሊገኙ የሚችሉ መኾናቸዉን መጠቆም እወዳለሁ።

ሙሉቀን አንዱዓለም (ዶ/ር) Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10662 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000 የሕይወት ሽግግሮች የጋራ ትዕምርቶች ትንተና በጃቢ ጠህናን ወረዳ ማህበረሰብ http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10663

አኅጽሮተ ጽሑፍ

ይህ ጥናት በጃቢ ጠህናን ወረዳ ማህበረሰብ ዘንድ የሕይወት ሽግግሮችን (ወሊድ፣ ጋብቻና ሞት) ምክንያት በማድረግ በሚፈጸሙ ሥርዓተ ክዋኔዎች (Rituals) ላይ ተደጋግመው የሚታዩ የጋራ የሆኑ ትዕምርቶችን (Symbols) መመርመር ላይ ያተኮረ ነው። የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች (Rites of Passage) ሲከበሩ መልካቸውን እየለዋወጡ የሚመጡና፣ በወቅቱ የሚገለጡ ትዕምርቶች መኖራቸው ሲሆን እነዚህንም ጉዳዮች በወጉ ያጠና ጥናት አለመኖሩ ነው። የጥናቱ ዋነኛ ዓላማ የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች ሲከበሩ ተደጋግመው የተገለጡ የጋራ ትዕምርቶችን መተንተን ነው። ለጥናቱ ግብዓት የሆኑ ቀዳማይ መረጃዎች ተጠኝው ማህበረሰብ ከተካለለባቸው አርባ አንድ ቀበሌዎች ውስጥ ስድስቱ በዓላማ ተኮር የንሞና ስልት የተመረጡ ሲሆን፣ አስር ሰዎች ደግሞ በቁልፍ መረጃ ሰጭነት ተሳትፈዋል። የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች ሲከናወኑ በመመልከትና ቃለ መጠይቅ በማካሄድ ተሰብስበዋል። ካልዓይ መረጃዎች ደግሞ ልዩ ልዩ ቤተ መጸሕፍትን፣ ድረ ገጾችንና ሰነዶችን በመጠቀም ተገኝተዋል። የጥናቱን መረጃዎች ለመተንተን ከተግባራዊ፣ ከመዋቅራዊ-ተግባራዊ እና ከፍካሬ ልቡናዊ ንድፈ ሀሳቦች ለዓላማዎች ተስማሚ የሆኑ ሀሳቦች ተመርጠው በማሕቀፍነት ተጠቅሟል። የተተነተነው መረጃ እንደሚያሳየው የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች (ወሊድ፣ ጋብቻና ሞት) የማህበረሰቡ እሴትና መዋቅር የሚገለጥባቸው፣ ተጠናክረውና ተጠብቀው የሚቀጥሉባቸው የሕይወት ዘመን ክስተቶች ናቸው። በአከባበር ሂደታቸው ወቅት በተለይ ሽግግሩን የሚያካሂደው ባለጉዳይ ጥበቃና እንክብካቤ የሚያስፈልገው መሆኑ፣ ማህበራዊነት ጎልቶ የሚታይባቸው እና የሰላምና የእርቅ ማውረጃና ማወጃ አጋጣሚዎች እንዲሁም የልዩ ልዩ መስዋዕት ማቅረቢያ ሁነቶች መሆናቸውን ማጤን ተችሏል። በተጨማሪም በጭንቀትና በስጋት የታጀቡ ሁነቶች መሆናቸው ሶስቱንም የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች ያስተሳሰሩ ትዕምርቶች መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

ቁልፍ ቃላት፡- [የሕይወት ሽግግር ሥርዓቶች፣ ሥርዓተ ክዋኔ፣ ትዕምርት]

ሥራዬ እንዳለው ውበቴ[1]፣ ዋልተንጉሥ መኮንን[2]፣ ደስታ አማረ[3] Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10663 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000 የወር አበባ ክልከላዎች እና ማኅበራዊ ተጽእኖዎቻቸው፦ በካፋ ዞን ማኅበረሰብ ተተኳሪነት http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10664

ይህ ጥናት ከወር አበባ ጋር የተያያዙ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማጥናት ላይ አተኩሯል። ዋና አላማው ከወር አበባ ጋር በተያያዘ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማህበራዊ ተጽእኖ ማሳየት ነው። ጥናቱ በካፋ ዞን በሚገኙ የካፋቾ፣ የናኦ እና የጻራ ብሔረሰቦች ላይ ተወስኗል። መረጃዎች ምልከታና ቃለ መጠይቅን በመጠቀም ተሰብስበዋል። በመረጃ ሰጪነት ወንዶችም ሴቶችም እንዲሁም ለመረጃ ማስተንተኛነት የማህበራዊ ውክልና ንድፈ ሀሳብ ተመርጠዋል። መረጃዎቹ እንደሚያመለክቱት አንዲት ሴት የወር አበባ ስታይ ከቤት ትወጣለች፤ ውሎዋና አዳሯ ከዋናው ቤት ውጪ በተሰራች አነስተኛ መጠለያ ውስጥ ይሆናል፤ እርሷ ያዘጋጀችውን ምግብ ሌላ ሰው አይመገብም፤ በተለይ እርሷ ያዘጋጀችዉን ምግብ ባለቤትዋ ከተመገበ ከባድ ችግር ይከሰታል ተብሎ ይታመናል። የወር አበባ እየታያት እቤት ውስጥ ከገባች ውቃቢ ይጣላታል፤ ልትታወር ትችላለች፤ ልትሞትም ትችላለች የሚል እምነት አለ። በመሆኑም በመኖሪያ ቤትዋ ውስጥ እያለች ድንገት የወር አበባ ቢታያት፣ ከቤትዋ ወጥታ ስትመለስ የመንጻት ሥርዓት እንዲፈጸምላትና ሁኔታዎችን እንድታመቻች ባህሉ ያስገድዳታል። በጥናቱ ውጤት መሰረት በተጠኑት ብሔረሰቦች ሴትነት በተለይ ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሀጥያት እና ንጹህ ያለመሆን ትዕምርት ተደርጎ ይወሰዳል። አንዲት ሴት የወር አበባ በምታይባቸው ቀናት ከቤተሰብ እንድትነጠል የሚያስገድደው ልማድ በመኖሩም ሴቷ በማኅበራዊም ሆነ በስነልቦና ረገድ የሚደርስባት ተጽእኖ ከፍተኛ ነው። የወር አበባ ለአቅመ ሄዋን የመድረስ መገለጫ ነው፤ ዘር ይቀጥል ዘንድ ተፈጥሮአዊ ጸጋ የሆነው የወር አበባ ሚናም የላቀ ነው፤ በመሆኑም ይህን ማኅበረሰቡ ተረድቶ ሴቶችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጉ በቤታቸው እንዲቆዩ አልያም መገለል እንዳይደርስባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በሚመለከታቸው አካላት ቢሰራ መልካም ነው።

የኔዓለም አረዶ[1]፣ ደስታ አማረ[2]፣ ደስታ ደሳለኝ[3] እና ፍሬሕይወት ባዩ[4]   Copyright (c) 2024 http://213.55.95.79/index.php/JAELC/article/view/10664 Tue, 05 Nov 2024 00:00:00 +0000